1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ለአፍሪካ በዴሞክራሲ በምሳሌነት ትቀጠስ የነበረችው ሴኔጋል ምን ገጠማት?

ረቡዕ፣ ጥር 29 2016

የሴኔጋል ፕሬዝደንት ማኪ ሳል በዚህ ወር መጨረሻ ሊካሔድ ቀነ ቀጠሮ ተቆርጦለት የነበረውን ምርጫ በማራዘማቸው በሀገሪቱ ተቃውሞ ተቀስቅሷል። ፕሬዝደንቱ ምርጫው እንዲገፋ የወሰኑት በሥልጣን ለመቆየት እንዳልሆነ ቢናገሩም እንደ መፈንቅለ መንግሥት የቆጠሩት አልጠፉም።

https://p.dw.com/p/4c8Xm
ተቃውሞ በሴኔጋል
የሴኔጋል ፖሊስ ለተቃውሞ አደባባይ የወጡ የተቃዋሚ ፖለቲከኞች ደጋፊዎችን በአስለቃሽ ጭስ ለመበተን ሞክሯል። ምስል Stefan Kleinowitz/AP/picture alliance

ለአፍሪካ በዴሞክራሲ በምሳሌነት ትቀጠስ የነበረችው ሴኔጋል ምን ገጠማት?

በምዕራብ አፍሪካዊቱ አገር ሴኔጋል በጎሮጎሳውያኑ አቆጣጠር የካቲት 25 ሊካሄድ የታቀደው ምርጫ እንዲተላለፍ እና ከአስር ወር በኋላ በመጪው ታህሳስ እንዲካሄድ መወሰኑ ሴኔጋላውያንን ለተቃውሞ አደባባይ አስወጥቷል። አለማቀፍ ማህብረሰቡንም ግራ አጋብቷል።

አገሪቱን ለሁለት ተከታታይ ጊዚያት ምርጫ አሸንፈው የመሩትና አሁን ግን ለሶስተኛ ግዜ እንደማይወዳደሩ ያስታወቁት ፕሬዝዳንት ማኪ ሳል፤ ባለፈው ቅዳሜ በብሄራዊው ቴሌቪዝን፤ ምርጫው የሚተላለፍ መሆኑን ማስታወቃቸው፤ ለብዙዎች እንግዳና ያልተጠበቀ ሲሆን፤ በርካቶችንም ወዲያውኑ ወደ አደባባይ ወተው ተቃውሟቸውን እንዲያሰሙ አድርጓቸዋል። ውሳኔውን ለማጽደቅ ሰኞ እለት የተሰበሰበው ፓርላማም ከፍተኛ ውርክብ የነበረበትና የተወሰኑ የፓርላማ አባላትም ከስብሰባው አዳራሽ እንዲወጡ ተገደው ውሳኔው ግን በአብላጫ ድምጽ ሊያልፍ እንደቻለ ተገልጿል።

ማኪ ሳል ለሦስተኛ ዘመነ ስልጣን አልወዳደርም አሉ

ፕሬዝዳንት ማኪ ሳል ባለፈው ቅዳሜ ምርጫው፤ የሚተለላለፍ መሆኑን ባሳወቁበት መግለጫቸው፤   በፕሬዝዳንሳዊ እጩዎችና የምርጫ አስፈጻሚ አካሎች መካከል የተፈጠሩት አለመግባባቶችና ውዝግቦች ከመፈታታቸው በፊት ምርጫ የማይካሄድ መሆኑን በመግለጽ፤ ችግሮቹ እንዲፈቱ የውይይት መድረኮችን የሚያዘጋጁ መሆኑን አታውቀዋል።

“በቅድሚያ ነጻና ትክክለኛ ምርጫ ለማካሄድ የሚያስችሉ ሁኒታዎችን ለመፍጠር የውይይት መድርኮችን አዘጋጃለሁ” በማለት ይህ ሳይሆን ምርጫው ቢካሄድ ግን በውጤቱም ላይ ውዝግብ ሊነሳና ሁከትም ሊፈጠር እንደሚችል አስታውቀዋል። በእርግጥ የምርጫው ጊዜ በተቃረበበት በአሁኑ ወቅት አንዳንድ እጩ ተወዳዳሪዎች በሙስና ወንጀሎች፤ ሌሎች ደግሞ የምርጫ ህጉን በመተላለፍና መስፈርቶችን ባለሟሟላት ምክኒያቶች  ከውድድር እንደታገዱ መደረጉ ጥሩ ያልሆነ ድባብ መፍጠሩ እየተነገረ ነው።

የሴኔጋል ፕሬዝደንት ማኪ ሳል
በሴኔጋል ተቃውሞ የተቀሰቀሰው በዚህ ወር ማብቂያ ሊካሔድ የታቀደ ምርጫ እንዲራዘም ፕሬዝደንት ማኪ ሳል በመወሰናቸው ነበር። ምስል Amr Alfiky/File Photo/REUTERS

ሆኖም ግን ፕሬዝዳንቱ ምርጫውን ለማስተላለፍ ያቀረቡትን ምክኒያትና ውሳኔያቸውን በርካቶች  ወዲያውኑ በዋና ከተማ ዳካርና በሌሎችም  ከተሞች ጭምር አደባባይ በመውጣት እንደትቃወሙት ነው የታወቀው። የፕሬዝዳንቱ እርምጃ እንደተባለው ሁኔታዎችን ለተሻለ የምርጫ ስራት ለማመቻቸት ሳይሆን የፖለቲካ አላማ ያለውና የአገሪቱንም ዴሞክራሲ አደጋ ላይ የሚጥል ነው በማለት ነው ብዙዎች አጥብቀው የተቃወሙት።

 አፍሪቃ መፈንቅለ መንግሥት የሚደጋገምባት ክፍለ ዓለም ሆናለች

የኢኮኖሚ ባለሙያና የፖሊስና ልማት የኢኮኖሚ ባላሙያዎች ማህበር ዳይሬክተር የሆኑት ሚስተር ንዶንጎ ሳምባ ስይላ ለመገናኛ ብዙሀን ሲናገሩ እንደተስሙት፤ የፕሬዝዳንቱ እርምጃ አስደንጋጭና የመንግስት ግልበጣ ያህል ነው፤ “ ውሳኔው ብዙዎችን ያስደንገጠ ነው። ፕሬዝድንቱ እንዳሉት ምክኒያቱ በተለያዩ የመንግስት አካሎች በተፈጠረው አለመግባባት ምክኒያት ምርጫው እንዳይታወክና ውጤቱም እንዳያወዛግብ ቢባልም እንኳ፤ ይህ የውስጥ ጉዳይ እንጂ ምርጫ እንዲተላለፍ የሚያስገድድ አይደለም” በማለት ይልቁንም ብዙዎቹ ስኔጋላውያን እርምጃውን የሲቪል የመንግስት ግልበጣ ወይም የህገመንግስት ሽረት አድርገው ነው የቆጠሩት  ብለዋል፤  የመንግስት ግለበጣዎች በመለዮ ለባሾች ብቻ ሳይሆን በስልጣን ላይ ባሉም ሊፈጸም እንድሚችል በማስታወስ ጭምር።

በሴኔጋል ተቃዋሚዎች
የሴኔጋል ፕሬዝደንት ማኪ ሳል ምርጫ እንዲራዘም በመወሰናቸው በሀገሪቱ ተቃውሞ ተቀስቅሷልምስል Seyllou/AFP

18 ሚሊዮን ህዝብ ያላት ሴኔጋል  እ እ እበ1960 አም ነጻነቷን ካገኘች ወዲህ ከብዙዎቹ ጎረቤቶቿ በተለየ ሁኔታ ምንም አይነት  መፍነቅለ መንግስት ያልተካሄደባትና ወደ ርስበርስ ጦርነትም ገብታ የማታውቅ፤ በዴሞክራሲ ልምምዷም ለሌሎች ያካባቢው አገሮች በምሳሌነት የምትጠቀስ ሆኖ ስላ፤ ይህ እርምጃ ግን ባለማቀፉ ማህብረሰብ ዘንድም ግርታን እንደፈጠረ ነው የሚታመነው፡፡የአውሮፓ ህብረት በቃል አቀባዩ በኩል የምርጫው መተላለፍ በስኔጋል አለመተማመንን ሊፈጥር እንደሚችል በማሳሰብ፤ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ግልጽና አካታች ምርጫ ሊካሄድ የሚችልበትን ሁኒታ ለመፍጠር እንዲሰሩ ጥሪ አቅርቧል።

የሴኔጋል ተቃውሞ የሀገሪቱን ምጣኔ ሀብት ይጎዳ ይሆን?

በአሜሪካ ምክርቤት የውጭ ግንኙነት ኮሚቴ ሰብሳቢ ሲናተር ቤን ካርዲን፤ የማራዘሙ እርምጃ ሴኔጋልን  ወደ አምባገነናዊ ስራት የሚመራት እንዳይሆን አስጠንቅቀዋል። የምዕራብ ዓፍሪካ የኢኮሚ ትብብር ኢኮዋስም የምርጫውን መተላለፍ መቃወሙ ተገልጿል። ይሁንና ኢኩዋስ  አባል መንግስታቱ  በመፈንቅለ መንግስት ህገመንግስታዊ ስራቱን ሲጥሱ ማስቆም ያላስቻለ ድርጅት በመሆኑ፤ በሴንጋል ላይ ተጽኖ ይፈጥራል ተብሎ አይታሰብም።

ፕሬዝዳንት ሳል ግን ዳግም በሰጡት መግለጫ፤ የሳቸው አላማ ሰላማዊና ተአማኒነት ያለው ምርጫ እንዲካሄድና የሴኔጋል ዴሞክራሲ እንዲጎለብት ለመስራት እንጂ፤ በተዘዋዋሪም ይሁን በቀጥታ ዳግም ወደስልጣን ለመምጣት አለመሆኑን አስታውቀዋል። ከተቃዋሚዎችም አንዳንዶች የምርጫውን መራዘም የሚደግፉ ሲሆን፤ በዚህም አንዳንዶች ሴኔጋል እንደተፈራው ሳይሆን ግልጽና ተአማኒ ምርጫ በማካሄድ ዴሞክርሲያዋን እንደምታስቀጥል ያላቸውን እመነት ይገልጻሉ።

ገበያው ንጉሴ

እሸቴ በቀለ

ሸዋዬ ለገሠ