1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ማኪ ሳል ለሦስተኛ ዘመነ ስልጣን አልወዳደርም አሉ

ማክሰኞ፣ ሰኔ 27 2015

የሴኔጋል ፕሬዝዳንት ማኪ ሳል ለሦስተኛ ዘመነ ስልጣን እንደማይወዳደሩ አስታወቁ። ትናንት ማታ ለዜጎቻቸዉ በብሔራዊ ቴሌቭዥን ጣብያ የቀጥታ ስርጭት ባደረጉት ንግግር፤ ፕሬዚዳንቱ ዳግም ምርጫ ላይ ለመሳተፍ ይፈልጋል የሚለውን ሰፊ ግምታዊ ሐሳብ ዉድቅ አድርገዋል።

https://p.dw.com/p/4TPOm
Frankreich | Senegals Präsident Macky Sall
ምስል Lewis Joly/AP/picture alliance

የሴኔጋል ፕሬዝዳንት ማኪ ሳል ለሦስተኛ ዘመነ ስልጣን እንደማይወዳደሩ አስታወቁ። ትናንት ማታ ለዜጎቻቸዉ በብሔራዊ ቴሌቭዥን ጣብያ  የቀጥታ ስርጭት ባደረጉት ንግግር፤ ፕሬዚዳንቱ ዳግም ምርጫ ላይ ለመሳተፍ ይፈልጋል የሚለውን ሰፊ ግምታዊ ሐሳብ ዉድቅ አድርገዋል። ሰኔ ወር መጀመሪያ ላይ በሃገሪቱ የታወቀዉ የተቃዋሚው መሪ ዑዝማኔ ሶንኮ በግፍ ፍርድ ቤት እስራት ከተፈረደበት በኋላ በአገሪቱ ውስጥ ከባድ አለመረጋጋት እና ተቃዉሞ ተቀስቅሶ ነበር ። የ61 ዓመቱ የሴኔጋል ፕሬዚዳንት የካቲት 25 ቀን 2024 ዓ.ም በሚካሄደው በቀጣዩ ምርጫ አልወዳደርም ሲሉ ይፋ ማድረጋቸዉ ሁኔታዉን ያበርደዋልተብሎ ይጠበቃል።ሳል ከጎርጎረሳዉያኑ 2012 ዓም ጀምሮ የምዕራብ አፍሪቃዊትዋን ሃገር ሴኔጋልን በአብላጫዉ ዴሞክራስያዊ ፓርቲ አባላት በሚገኙበት ሃገሪቱን አስተዳድረዋል።  

አዜብ ታደሰ 

ኂሩት መለሰ