1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የለውጥ ፍላጎት በሰኔጋል ምድር

ሐሙስ፣ መጋቢት 19 2016

``ሕዝቡ ለባሲሩ ዲዮማዬ ፋዬ በይፋ ድምጹን ሰጥቷል። ይህ የሆነው ግን በዑስማን ሶንኮ ዋስትና ሰጪነት ነው። እሱ ማለት ባሳርዮ ፋዬን የመለመለና በእውነቱ የምርጫ ዘመቻውን የደገፈ፤ እንዲሁም አጠቃለይ የፖለቲካ ፕሮጀክቱን የሚደግፍ ሰው ነው።``

https://p.dw.com/p/4eE2m
ሚስተር ዲዮማየ
አዲሱ የሰኔጋል ተመራጭ ሚስተር ዲዮማየ ፋዬምስል Luc Gnago/REUTERS

የሰኔጋል ምርጫና የለውጭ ፍላጎት


በሰኔጋል የምርጫ ዘመቻው ወቅት ዲዮማያ ፋዬ "የስርዓት ለውጥ እጩ" እና "የግራ ክንፍ ፓን አፍሪካኒዝም" ተወካይ መሆናቸውን ገልጸዋል ። የገንዘብ ፖሊሲ ማሻሻያዎችን ለማድረግና  የነዳጅና የማዕድን ውሎችን እንደገና በመከለስ እንደሚሰሩ በመቀስቀሳቸው በሴኔጋል በተለይም በወጣቶቹ ዘንድ ለውጥ ይመጣል የሚል ተስፋ ሰንቋል ።
ፋዬ የሴኔጋል "ሉዓላዊነት" እንደሚመለስ ፣ ሙስናን በቁርጠኝነት እንደሚዋጉ ፣ በአገሪቱም ፍትሐዊ የሀብት ክፍፍል እንደሚሰፍን ቃል ገብቷል ።
ተንታኞች ደግሞ  ይህን ያሉት ሴኔጋልን ከምዕራባውያን ኃይሎች በተለይም ደግሞ ከቀድሞዋ የቅኝ ገዥ ከፈረንሳይ ለማራቅ በማሰብ እንደሆነ ይናገራሉ ።
የሴኔጋልን ከፍተኛ ሥልጣን በይፋ ሊይዝ የተቃረበው ፋዬ ፖለቲካዊ ብልሹነትን ለመዋጋት ቅድሚያውን ወስዷል ። በተጨማሪም የሴኔጋልን ኢኮኖሚ ለማስተካከል ከሚወስዱአቸው የገንዘብ ፖሊሲዎች አንዱ ተቺዎች በፈረንሳይ ግምጃ ቤት ቁጥጥር ስር ውሏል የሚሉትን የሃገሪቱ  ሲ ኤፍ  ፍራንክ የተባለውን የሃገሪቱ ገንዘብ ከዚህ ተጽዕኖ ሥር ማላቀቅን  ይገኝበታል ።
በሰኔጋል የኦፕን ሶሻይቲ የአፍሪቃ ተነሳሽነት ዳይሬክተር ሐዋ ባ ለዶቸቨለ በሰጡት አስተያየት ተከታዩን ብለዋል።

`` አሁን እየተከሰተ ያለው የመጀመሪያው ለውጥ ከዜጎቻችንና ተቋማት ጋር ጨካኝ ፣ በጣም ጨካኝና ግልፍተኛ የነበረውን የፖለቲካ ክፍል በማጥፋት ላይ... ከፕሬዚዳንት ዲዮማዬ ፋዬ የሚጠበቀው ዋናው አቀራረብ የዴሞክራሲ ተቋሞችን መመለስ ነው ።``
እንደሐዋ እምነት አዲሱ ፕረዚደንት ለመሆን እያኮበኮቡ ካሉት ፋዬ የዴሞክራሲያዊ ተቋማት ግንባታ፣ የፕረዚደንቱን ስልጣን መገደብና የዜጎች ተሳትፎ ማሳደግ ላይ ተግተው እንደሚሰሩ ተስፋ አድርጋለች።
የፋየን የፕረዚደንትነት የምርጫ ሂደት ያጀቡት የፓርቲው አጋራቸው ኦሳማን ሶንኮ በምርጫው የቅስቀሳ ፖስተር ሁለቱም ጎንለጎን በያዘ ምስል ላይ ``ዲሞያ ፋዬ ማለት ሶንኮ ነው`` የሚል ጽሑፍ መለጠፉ ምናልባት የሶንኮ ደጋፊዎች ድምጻቸውን ለፋዬ እንዲሰጡ ለማሳሰብ ሳይሆን እንደማይቀር ብዙዎች ገምተዋል። ምክንያቱም ሶንኮ በፍርድቤት በቀረበባቸው ክስ ምክንያት ከፕረዚደንታዊ የምርጫ ውድድር ውጭ በመሆናቸው ነው።

 የሰኔጋል ፕረዚደንታዊ ምርጫ በከፊል
የሰኔጋል ፕረዚደንታዊ ምርጫ በከፊልምስል Luc Gnago/REUTERS


የምርጫ ውጤቱ በመጪው አርብ በይፋ የሚገለጽ ቢሆንም ቀድመው የወጡ የምርጫ ውጤት ሪፖርቶች እንዳመላከቱት 7 ሚሊዮን ከሚሆነው የሴነጋልመራጭ ህዝብ የገዥው ፓርቲ እጩ የሆኑት ጠቅላይ ሚኒስተር ባ 36.2 ከመቶ ድምጽ ሲያገኙ፤ ሚስተር ዲዮማየ 53.7 ድምጽ በማገኘት ሁለተኛ ዙር ውድድር ሳያስፈልጋቸው አሸናፊ ሆነዋል።
ሚስተር ዲዮማየ ፋዩ አሸናፊነታቸው የገለጹ ሲሆን አንዳንድ ተቃዋሚዎችም ከወዲሁ እንኳን ደስ ያለዎት ማለት ጀምረዋል።  ፋዬ ለደጋፊዎቻቸው ባሰሙት ንግግርም “ አገሬን በታማኝነትና ግልጽነት ለማገልገል እጥራለሁ፤ በየትኛውም ደረጃ ያለውን ሙስናም እዋጋለሁ፤ የዴሞክራሲ ተቋሞችንም እንደገና እገነባለሁ” ሲሉ ተደምጠዋል።
በጀርመን ፍሬዴሪሽ ኤቨርት ፋውንዴሽን የሰኔጋል ዳይሬክተር የሆኑት ኢስማኢል ዲካ ለዶይቸቨለ በሰጡት ማብራሪያ

``ሕዝቡ ለባሲሩ ዲዮማዬ ፋዬ በይፋ ድምጹን ሰጥቷል። ይህ የሆነው ግን በዑስማን ሶንኮ ዋስትና ሰጪነት ነው። እሱ ማለት ባሳርዮ ፋዬን የመለመለና በእውነቱ የምርጫ ዘመቻውን የደገፈ፤ እንዲሁም አጠቃለይ የፖለቲካ ፕሮጀክቱን የሚደግፍ ሰው ነው።`` 

በሰኔጋል ፕረዚደንታዊ ምርጫ መራጮች ድምጽ ሲሰጡ
በሰኔጋል ፕረዚደንታዊ ምርጫ መራጮች ድምጽ ሲሰጡምስል Marco Longari/AFP

በምህጻሩ PASTEF እየተባለ የሚጠራው ተቃዋሚ ፓርቲ እንደጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር በ2014 ሲመሰረት የግብር ሰብሳቢ መስሪያቤት ዋና ዳይሬክተር የነበሩትፉዬ ታዋቂ የፓርቲው አመራር አባል ለመሆን ጊዜ አልወሰደባቸውም። እንደጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር የትግል አጋራቸው ሶንኮ ሲታሰሩ ፉዬ የፓርቲው ዋና ጸሐፊ ለመሆን በቅተዋል። እኒህ ጓደኛሞች እንደሆኑ የሚነገርላቸው ፖለቲከኞች ሶንኮ ሲታሰሩም  እሳቸውን ተክተው የሚወዳደሩ ዕጩ ፉየ መሆናቸውን አሳወቁ።  የሶንኮ መሰፈታት እርግጠኛነት ማወቅ ባለመቻሉ ፓርቲው በ2024 ምርጫ፤ ፓርቲውን ወክለው የሚወዳደሩት ፋዬ መሆናቸውን አጸደቀ። በሃገሪቱ ፖለቲካ የሶንኮ ሚና የጎላ ቢሆንም የሰኔጋላውያን ሕይወት በመቀየር ሁለቱም በጋራ እንደሚሰሩ ነው በጀርመን ፍሬዴሪሽ ኤቨርት ፋውንዴሽን የሰኔጋል ዳይሬክተር የሆኑት ኢስማኢል ዲካ የሚገልጹት።

``ለሴኔጋል ሕዝብ ያሳዩትና የሸጡት  ማኅበራዊ ጽንሰ ሐሳብ ለሰኑጋል ሕዝብ ችግሮችን ለመፍታት አብረው እንደሚሰሩ የሚያሳይ ነው። ``
 በሁለቱም ፖለቲከኞች የወደፊት የትብብር ፈንታ እስከአሁን ግልጽ አደለም። የፕሬዚደንቱ ስልጣን ይገደብ፤ አልያም የስልጣን ክፍፍሉ ምን ሊሆን እንደሚችል ገና በውል አልለየም።  በሰኔጋል የኦፕን ሶሻይቲ የአፍሪቃ ተነሳሽነት ዳይሬክተር ሐዋ ባ፤ ሶንኮ በመጪው መንግስት የጠቅላይ ሚኒስትርነት አልያም ተመጣጣኝ ቦታ ሊሰጣቸው እንደሚችል ግምቷን ሰጥታለች።

ዮሃንስ ገብረግዚአብሄር

ማንተጋፍቶት ስለሺ