1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ህዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ የወደፊት እቅድ

ሰኞ፣ መስከረም 14 2011

የኢትዮጵያ ህዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ፣ ኢህአፓ ከ46 ዓመት በኋላ ባለፈው የሳምንት መጨረሻ አዲስ አበባ ገብቷል። ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ በውጪ ያሉ የተለያዩ ፖለቲካ ፓርቲዎች ለአገር ግንባታ ወደ አገር እንዲገቡ ያደረጉትን ጥሪ ተከትሎ ነው ከፍተኛው የፓርቲው አመራር ቡድን ሰሞኑን ወደ ሀገር የተመለሰው።  

https://p.dw.com/p/35PcX
Karte Äthiopien englisch

ኢህአፓ

ከአራት አሰርተ ዓመት በላይ በኋላ ወደ ሀገር ቤት የተመለሰው ኢህአፓ በአጭር ጊዜ እቅዱ መሰረት በዓብዮቱ ጊዜ ከኢህአፓ ጋር በተያያዘ ይሰሩ ከነበሩ ህዝባዊ ድርጅቶች ጋር ሲንቀሳቀሱ ጉዳት የደረሰባቸውን አፈላልጎ የችግራቸው ተካፋይ መሆኑን ለመግለጽ እና ለተሰሩ ስህተቶችም ይቅርታ ለመጠየቅ እንደሚፈልግ የከፍተኛው ቡድን መሪ አቶ ማስረሻ ዮሴፍ ለDW ገልጸዋል። በመካከለኛ ጊዜም ፓርቲው ከህብረተሰቡ ጋር በዓላማ እና በፖለቲካ ላይ የተመሰረተ ውይይት እያካሄደ የፖለቲካ ስራውን የመጀመር እቅድ እንዳለውም አቶ ማስረሻ አክለው አስታውቀዋል።

ገበያው ንጉሤ

አርያም ተክሌ

ሸዋዬ ለገሠ